ውድ በሂውስተን ከተማና አካባቢ ነዋሪ ወገኖቻችን በሙሉ፥
የኮሮና ቫይረስ ድንገተኛ ክስተት ያስከተለውን ቀውስ ተከትሎ የሂውስተን ከተማና አካባቢዋ አስተዳደር ለሚቀጥሉት 7 ቀናት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ አውጥቷል። በዚህም ምክንያት ከቫይረሱ ባሕሪ አኳያ ባሁኑ ሰዓት ማንኛውም ሕዝባዊ ስብሰባ ግለሰቦችን ለቫይረሱ ሊያጋልጥ ይችላል ከሚለው የባለሞያዎች ማስጠንቀቂያ በመነሳት እንዲሁም ለወገኖቻችን ጤንነትና ደህንነት ከፍተኛ ግምት በመስጠት በፊታችን ቅዳሜ March 14 ልናከብር የነበረውን የአድዋ በዓል መርሃ ግብር መሰረዛችንን ስናሳውቃችሁ በታላቅ ኀዘን ነው። ይህንን ውሳኔ ለማድረግ ቀላል እንዳልነበረና ብዙ ያሰብንበትና የተወያየንበት መሆኑን እንደምትረዱልን ይልቁንም ከጊዜው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አገናዝባችሁ በውሳኔው እንደምትደግፉን ተስፋ እናደርጋለን።
— የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ አንድነት ማህበር አመራር
የአድዋ በዓል ዝግጅት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተሰረዘ!
- Post author:ecohadmin
- Post published:March 12, 2020
- Post category:Community News