ባለፈው እሁድ March 10, 2019 በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው ያለፉትን 157 መንገደኞች ለማስታወስ እሁድ March 17 በሂውስተን ከተማ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ አንድነት ማሕበር ባዘጋጀው የጸሎትና የሻማ ማብራት ሥነስርዓት ላይ ብዙ ኢትዮጵያውያኖችና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ተገኝተው የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገልጸዋል። በዚሁም ሥነስርዓት ላይ የኃይማኖት አባቶች ተገኝተው ታዳሚውን በምክርና በጸሎት ያጽናኑ ሲሆን የአደጋው ሰለባ ለሁኑት ከ36 አገራት የተውጣጡ ተሳፋሪዎችና የአውሮፕላኑ ሰራተኞችን በማስታወስ 36 ነጭ ፊኛዎችና አንድ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ጥንድ ፊኛ ወደሰማይ የተለቀቁ ሲሆን በመቀጠልም የሻማ ማብራት ሥነስርዓት ተካሂዷል። በዚህ አጋጣሚ ማሕበሩ በሥነስርዓቱ ላይ በመገኘት ወገናዊ አንድነታቸውንና ድጋፋቸውን ለገለጹት የማሕበረሰቡ ዓባላት ሁሉ ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀርባል!
Candlight vigil in memory of the 157 lives lost on Ethiopian Airlines flight # 302 on March 10, 2019 was held on Sunday March 17, 2019 at the Bayland Park in Houston, Texas. The event was attended by many Ethiopians and friends of Ethiopia in the greater Houston area. Among the attendees were leaders from the local Ethiopian Orthodox Church and Ethiopian Evangelical Church as well as the Muslim Community. The event was highlighted by prayers and release of balloons representing the passengers from the 36 nations and the crew aboard the flight. The Ethiopian Community Organization, who organized the event, would like to thank all the attendees for taking their time to come out and show their support and solidarity in this time of difficulty.