ስለአባይ አይነተኛ ጥያቄ ቢሰነዘርብዎ አጥጋቢና ትክክለኛ መልስ መስጠት ይችላሉ? እርግጠኛ ካልሆኑ ወደዚህ ሁለተኛው ዙር የትምህርታዊ መድረክ ይምጡ! በዓባይ ዙሪያ ያለውን ታሪካዊ ዓለማቀፋዊ ኢኮኖሚያዊ ሕጋዊና ዲፕሎማሲያዊ እንድምታ እንዲሁም የግድቡን ምሕንድስና ወቅታዊ ሒደትና ሁለተኛውን ሙሊት በተመለከተ በመስኩ የታወቁ ባለሙያዎች ጥያቄዎን ለመመለስና ግንዛቤዎን ለማስፋት ተዘጋጅተው እንደገና ይጠብቁዎታል።