ውድ ወገኖቻችን በከተማችን በሂውስተንና አካባቢው የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ አራት (4) ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት ተከፍተዋል። በቫይረሱ የመያዝ ስሜት የሚሰማው ግለሰብ ወደነዚህ ጣቢያዎች በመሄድ ምርመራውን ማግኘት ይችላል። ይህ ምርመራ ኢንሹራንስ ለሌላቸውና የመክፈል አቅም ለሌላቸው ነፃ ሲሆን መክፈል ለሚችሉ እንደአቅማቸው፣ ኢንሹራንስ ላላቸው ደግሞ ያለ ኪስ ወጪ ክፍያ ይሰጣል። ከመሄድዎ በፊት በስልክ ቁጥር (832) 548-5226 በመደወል ጣቢያው የሚጠይቀውን የቅድመ ምርመራ ጥያቄዎች ይመልሱ። የምርመራ ጣቢያዎቹ አድራሻ እንደሚከተለው ነው፥
Legacy Fifth Ward, 3811 Lyons Ave.
Legacy Montrose, 1415 California St.
Legacy Southwest, 6441 High Star Dr (Next to ECOH office)
Drive Through Testing:
Memorial Medical Center, 510 West Tidwell
ተጨማሪ የምርመራ ጣቢያዎች በሂውስተን ከተማና አካባቢዋ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚከፈቱ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። መረጃው እንደደረሰን በFacebook ገጻችን እናሳውቃለን።