ባለፈው March 2, 2019 የ123ኛው ዓመት የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሂውስተን ከተማ በሚገኙ ኢትዮጵያውያኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያኖች እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆችና እንግዶች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል። በዚሁም ዝግጅት ላይ ዶክተር ኃይሌ ላሬዶ እና ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም የአድዋን ድል ታሪክ በስፋትና በጥልቀት የተመለከቱ ሲሆን አያይዘውም የአድዋ ድል አሁን ላለውና ለሚመጣው ኢትዮጵያዊ ትውልድ አንድት እድገትና አገራዊ ሉዓላዊነት እንዲሁም የጥቁርን ህዝብ ነጻነትና ህልውና በማስከበር ረገድ ያመጣውንና የሚያመጣውን ተጽህኖ ለበዓሉ ታዳሚዎች አስረድተዋል። በበዓሉ ላይ ተካፋይ ከነበሩትም የመንግስት ተወካይ እንግዶች መካከል Congress Woman Sheila Jackson የአድዋ ድል የኢትዮጵያኖች ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ እና የጥቁር አሜሪካኖች ድል መሆኑን እና እጅግ የሚኮሩበት ታሪክ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህንንም ቀን የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ይሁን በማለት በ US Congress የረቀቀውን አዋጅ (proclamation) ለማሕበሩ አበርክተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በዝግጅቱ ላይ ቀርበው የነበሩት የባህል ዘፈኖች ፣ ሥዕላዊ ኤግዚቢሽኖች ፣ ግጥሞች እና ባህላዊ ምግቦች ለባዓሉ ከፍ ያለድምቀት ሰጥተውታል። See more pictures from the event: https://www.flickr.com/…/143825255…/albums/72157706187244581